አብዛኞቻችን ዘመናዊ ሶፍትዌሮችን እንጠቀማለን፣ ነገር ግን እንደ ኦፊስ 2021 ያሉ የጽሕፈት መገልገያዎች በአሮጌው ፓወር ግእዝ አይሰሩም፤ ለአጠቃቀም አስቸጋሪነቱ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። የማክሮሶፍት ዊንዶውስ ግቤትም ምቹና ያልተለመደ ነው። ይህን ችግር ለመቅረፍ ፕሮ ግእዝ የተባለ ዘመናዊና ተመራጭ የግቤት ሶፍተዌር እነሆ ብለናል። በፓወር ግእዝና ሌሎች ግቤቶች ያልነበሩ ድቃላና ኅፁፃን ፊደላት፣ የልዩ ልዩ ቋንቋ ፊደላት፣ የግእዝ ቁጥሮች፣ ሥርዓተ ነጥቦች እና የዜማ ምልክቶች በቀላሉ መጻፍ በሚቻልበት መንገድ ተካተዋል።
Features
- ባለብዙ ቋንቋ ድጋፍ፦ ግእዝ፣ ትግርኛ፣ ትግሬ፣ አማርኛ፣ ጉራጊኛ፣ አገውኛ፣ ኸምጠኛ፣ ሀረሪ፣ አርጎባ፣ ሲልጤ፣ ዛይ እና የሌሎችንም ተመሳሳይ ቋንቋዎች የፊደል ገበታ በዋናው የቁልፍ ሰሌዳ ላይ በማካተት ቀርቧል።
- ምቹ አጠቃቀም፦ ኮምፒውተርዎ ላይ ወርድ፣ ኤክሴል፣ ኖትፓድ እና ስቲኪ ኖት እና የመሳሰሉት ላይ ፋይሎችን እና ማህደሮችን በሀገርኛ ቋንቋ መፈለግ፣ መሰየምና ማስተካከል እንዲሁም በድረ ገጾች፣ ዩቲዩብ፣ ቴሌግራም፣ ፌስቡክ መተግበሪያዎች ላይ በቀጥታ በሀገርኛ ቋንቋ መጻፍና መረጃዎችን መፈለግ ያስችላል።
- የዜማ ምልክቶች፦ ፕሮ ግእዝ የቅዱስ ያሬድን የዜማ ምልክቶችን በመያዙ የዜማ መጻሕፍትን ለማመልክት ያግዛል።
- ቀላል የአጻጻፍ ዘዴ፦ ጥናት ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀው ፕሮ ግእዝ አነስተኛ የቁልፍ ጥምረቶችን ይጠቀማል። ለምሳሌ "ቧ" ለመጻፍ "b" + "aa" የሚሉትን ሁለት ቁልፎች ብቻ መጫን በቂ ነው።
- ለሶፍትዌር ገንቢዎች ምቹነት፦ የሶፍትዌር ገንቢዎች አፕሊኬሽኖችን በሀገርኛ ቋንቋ ለማበልጸግ ሲፈልጉ በቀጥታ በፕሮግራማቸው ላይ መጻፍ ይችላሉ።
- ለሁሉም የዊንዶውስ ሥሪቶች ተኳኋኝ ነው።
Categories
Software DistributionOther Useful Business Software
Our Free Plans just got better! | Auth0
You asked, we delivered! Auth0 is excited to expand our Free and Paid plans to include more options so you can focus on building, deploying, and scaling applications without having to worry about your security. Auth0 now, thank yourself later.
Rate This Project
Login To Rate This Project
User Reviews
Be the first to post a review of Pro Ge'ez IME!