አብዛኞቻችን ዘመናዊ ሶፍትዌሮችን እንጠቀማለን፣ ነገር ግን እንደ ኦፊስ 2021 ያሉ የጽሕፈት መገልገያዎች በአሮጌው ፓወር ግእዝ አይሰሩም፤ ለአጠቃቀም አስቸጋሪነቱ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። የማክሮሶፍት ዊንዶውስ ግቤትም ምቹና ያልተለመደ ነው። ይህን ችግር ለመቅረፍ ፕሮ ግእዝ የተባለ ዘመናዊና ተመራጭ የግቤት ሶፍተዌር እነሆ ብለናል። በፓወር ግእዝና ሌሎች ግቤቶች ያልነበሩ ድቃላና ኅፁፃን ፊደላት፣ የልዩ ልዩ ቋንቋ ፊደላት፣ የግእዝ ቁጥሮች፣ ሥርዓተ ነጥቦች እና የዜማ ምልክቶች በቀላሉ መጻፍ በሚቻልበት መንገድ ተካተዋል።

Features

  • ባለብዙ ቋንቋ ድጋፍ፦ ግእዝ፣ ትግርኛ፣ ትግሬ፣ አማርኛ፣ ጉራጊኛ፣ አገውኛ፣ ኸምጠኛ፣ ሀረሪ፣ አርጎባ፣ ሲልጤ፣ ዛይ እና የሌሎችንም ተመሳሳይ ቋንቋዎች የፊደል ገበታ በዋናው የቁልፍ ሰሌዳ ላይ በማካተት ቀርቧል።
  • ምቹ አጠቃቀም፦ ኮምፒውተርዎ ላይ ወርድ፣ ኤክሴል፣ ኖትፓድ እና ስቲኪ ኖት እና የመሳሰሉት ላይ ፋይሎችን እና ማህደሮችን በሀገርኛ ቋንቋ መፈለግ፣ መሰየምና ማስተካከል እንዲሁም በድረ ገጾች፣ ዩቲዩብ፣ ቴሌግራም፣ ፌስቡክ መተግበሪያዎች ላይ በቀጥታ በሀገርኛ ቋንቋ መጻፍና መረጃዎችን መፈለግ ያስችላል።
  • የዜማ ምልክቶች፦ ፕሮ ግእዝ የቅዱስ ያሬድን የዜማ ምልክቶችን በመያዙ የዜማ መጻሕፍትን ለማመልክት ያግዛል።
  • ቀላል የአጻጻፍ ዘዴ፦ ጥናት ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀው ፕሮ ግእዝ አነስተኛ የቁልፍ ጥምረቶችን ይጠቀማል። ለምሳሌ "ቧ" ለመጻፍ "b" + "aa" የሚሉትን ሁለት ቁልፎች ብቻ መጫን በቂ ነው።
  • ለሶፍትዌር ገንቢዎች ምቹነት፦ የሶፍትዌር ገንቢዎች አፕሊኬሽኖችን በሀገርኛ ቋንቋ ለማበልጸግ ሲፈልጉ በቀጥታ በፕሮግራማቸው ላይ መጻፍ ይችላሉ።
  • ለሁሉም የዊንዶውስ ሥሪቶች ተኳኋኝ ነው።

Project Activity

See All Activity >

Follow Pro Ge'ez IME

Pro Ge'ez IME Web Site

Other Useful Business Software
$300 Free Credits to Build on Google Cloud Icon
$300 Free Credits to Build on Google Cloud

New customers can spin up VMs, build with AI, and query data at no cost.

Put your $300 in credit toward real workloads, then keep building with free monthly usage for 20+ products. No commitment and no charge until you upgrade.
Start Free
Rate This Project
Login To Rate This Project

User Reviews

Be the first to post a review of Pro Ge'ez IME!

Additional Project Details

Registered

2025-03-03